ኢትዮጵያ የ4 ቢሊዮን ዶላሩን የዚጂን ጎልድ እና የአላይድ ጎልድ የባለቤትነት ሽግግር አጸደቀች

የኢትዮጵያ መንግሥት የቻይናው ዚጂን ጎልድ ኢንተርናሽናል የካናዳውን አላይድ ጎልድ ኮርፖሬሽን በ4 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ያቀረበውን ጥያቄ አጽድቋል። ይህ ውሳኔ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘውን የኩርሙክ ወርቅ ማውጫ ፕሮጀክት በይፋ ለመጀመር ትልቅ በር ከፍቷል።

ባለፈው ጥር ወር ይፋ የተደረገው ይህ ግብይት፣ የአላይድ ጎልድን ዓለም አቀፍ የሥራ ድርሻ ወደ ዚጂን ጎልድ የሚያዞር ነው። ካፒታል ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበዉ የባለቤትነት ለውጡ ቢኖርም የፕሮጀክቱ የሥራ ሂደት እንደማይስተጓጎል አረጋግጧል።

በ620 ሚሊዮን ዶላር የተገነባው የኩርሙክ ማውጫ፣ በዓመት 290 ሺህ አውንስ ወርቅ የማምረት አቅም ያለው ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ትልቁ ዘመናዊ የወርቅ ማውጫ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ማዕድኑ በዓለም ላይ ካሉ ዝቅተኛ የወጪ ምርት ካላቸው ማውጫዎች አንዱ እንደሚሆን ተገምቷል።

የዘርፉ ባለሙያዎች፣ እንደ ዚጂን ጎልድ ያሉ ዓለም አቀፍ ግዙፍ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው በዘርፉ ላይ ያለውን ኢንቨስተሮች የመተማመን አቅም እንደሚያሳድግ ገልጸዋል።seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories