በግንባታው ዘርፍ በጥራት እና በልህቀት ከ20 ዓመታት በላይ የተሻገረውና የባማኮን ግሩፕ አካል የሆነው ባማኮን ሪልስቴት መሐል ቦሌ ላይ ያስገነባቸውን ቅንጡ እና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የመኖሪያ አፓርታማዎችን ለደንበኞቹ በገባው ውል መሰረት ዛሬ አስረክቧል።
ለደንበኞች የተላለፈው አፓርታማ ከቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፊትለፊት መገኘቱ በተለይ ለዓለም አቀፍ ተጓዦች እጅግ ተመርጭና ተፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ቤቶቹ በተመጣጣኝ ዋጋ እንደቀረቡና ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ የተጠናቀቁ እንደሆነ የባማኮ ሪል ስቴት ሽያጭና ማርኬቲንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ፍሬው በየነ አስታውቀዋል፡፡

ባማኮን ለቤት ባለቤቶቹ ያስረከብናቸው አፓርታማዎች፣ በአንድ ወለል ላይ ሁለት ሱፐር ሌግዘሪ ቤቶችን የያዙ እንደሆኑ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ባማኮን ሪልስቴት ከመሠረት እስከ መጨረሻው ማሳመሪያ (Finishing) ድረስ ግንባታዎቹን በራሱ በባማኮን ግሩፕ እህት ኩባንያዎች (ባማኮን ሪል እስቴት፣ አንከር ፋውንዴሽን ስፔሻሊስት፣ ባማኮን ኢንጅነሪንግ፣ አልፋ ፖስት ቴንሽኒንግ፣ ባማ ሚክስ ኮንክሪት፣ ታወር ኢንጅነሪንግ፣ አልትሜት ኬሚካልስ እና ፊት አውት ኮንስትራክሽን) በጥምረት እንደሚያከናውን ያስታወቁት አቶ ፍሬው ይህም ቤቶቹን በከፍተኛ ፍጥነት፣ በአስተማማኝ ጥራት ለመስራት እንዳስቻለው ተናግረዋል፡፡
በሪልስቴት ዘርፉ አዳዲስ የፈጠራ እና የልህቀት መመዘኛዎችን በመተግበር በምሥራቅ አፍሪካ መሪ የመሆን ራእይ ሰንቆ እየሰራ ነው ያሉት አቶ ፍሬው ኩባንያው በአሁኑ ወቅት በካዛንችስ፣ ባምቢስ፣ አትላስ፣ ፍሬንድሺፕ ፓርክ፣ ቦሌ ኤርፖርት ቪው፣ ሜክሲኮ እና ቡልቡላ “ሳይቶች” ላይ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በከፍተኛ ጥራት እና ፍጥነት እየገነባ ይገኛል ብለዋል።seco


