በአለምሰገድ እስጢፋኖስ
ካምፓኒው የደንበኞቹ ቁጥር 90 ነጥብ 1 ሚሊየን መድረሱን አስታውቋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የካምፓኒውን የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ላይ እንዳስታወቁት ኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ ገቢ ያገኘው ከዳታ/ ኢንተርኔት አገልግሎት ነው።
ለዓመታት ከድምፅ አገልግሎት ከፍተኛ ገቢ ሲያገኝ የቆየው ኩባንያው አሁን 31.1% ከዳታ፣ 23.5% ከድምፅ ሲያገኝ አጠቃላይ ገቢው 215 ቢሊየን ብር መሻገሩን አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት በማቅረብ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየሰራ ነው፡፡
አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር በገጠርና በከተማ የመረተ ልማት ዝርጋታ በማከናወን ተደራሽነቱን የማስፋት ስራ ተከናውኗል፡፡

በገጠር አካባቢዎች 117 ወረዳዎች የኔትወርክ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች ተጠቃሚ ማድረግ ሲቻል 246 ተጨማሪ ከተሞች የ4ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ 7 ከተሞች የ5ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ፍሬህይወት ታምሩ አስታውቀዋል፡፡
በከተማና በገጠር በተከናወሰ ስራ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 90 ነጥብ 1 ሚሊየን መድረሱን ጠቁመዋል።
በበጀት አመቱ ካምፓኒው 215 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ 215 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቀዋል። የተገኘው ገቢ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር 33 ነጥብ 2 በመቶ ብልጫ እንዳለው ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል።
በዓመቱ ዲጂታል ፋይናንስን በማጠናከር ቀልጣፋና አካታች አገልግሎት ለመስጠት መሰራቱን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ
አሁን ላይ የቴሌብር ደንበኞች ቁጥር 60 ነጥብ 6 ሚሊየን ሲደርስ በበጀት ዓመቱ በቴሌብር 4 ነጥብ 51 ትሪሊየን ብር ግብይት መፈጸሙን አስታውቀዋል፡፡seco


