የዓለም ሁለተኛው ትልቁ የኮንቴይነር መርከብ ድርጅት የሆነው ኤ.ፒ. ሞለር-ማርስክ በቀይ ባህር ውስጥ በንግድ መርከቦች ላይ ከደረሰው ጥቃት በኋላ ለሦስት ዓመታት ያህል ተቋርጦ የነበረውን የሱዌዝ ካናል አገልግሎት በከፊል እያስጀመረ መሆኑ ተገልጿል።
የዴንማርኩ ግዙፍ የባህር ትራንስፖርት ኩባንያ፣ ከጀርመኑ ሃፓግ-ሎይድ ጋር በጋራ የሚያከናውነውን የኤኤ15 (AE15) የእስያ-አውሮፓ መስመር አገልግሎት እንደሚያድስ ካስታወቀ ቀናት ባልሞሉ ጊዜ ውስጥ፣ የመካከለኛው ምስራቅ-ዩኤስ ምስራቅ ጠረፍ አገልግሎቱን በሱዌዝ ካናል በኩል እንደሚመልስ አስታውቋል።
ይህ የቅርብ ጊዜ ውሳኔ፣ በየመን የሁቲ አማጽያን ጥቃት አብዛኛዎቹን ዓለም አቀፍ የመርከብ መስመሮች መርከቦቻቸውን በአፍሪካ የኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ ዙሪያ እንዲያዞሩ ካስገደዳቸው ከ2023 መጨረሻ ወዲህ ተትቶ የነበረውን መስመር ቀስ በቀስ ለመክፈት የተወሰደ ሌላ እርምጃ ነው።
ኩባንያው ወደ አጭሩ የሱዌዝ መስመር መመለሱ በኤምኢሲኤል አገልግሎት በምዕራብ አቅጣጫ የሚደረገውን የጉዞ ጊዜ በአማካይ በሰባት ቀናት እንደሚቀንሰው፣ በምስራቅ አቅጣጫ የሚደረገው ጉዞ ደግሞ በደቡባዊ አፍሪካ ዙሪያ ከመጓዝ እስከ 14 ቀናት እንደሚፈጥን ገልጿል።seco


