ኢትዮቴሌኮም  ለሚያለማቸው መሬቶች እና ችግኞች  ከ159 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መድቦ እየሰራ እንደሚገኝ የካምፓኒው ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይዎት ታምሩ አስታወቁ

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ

  በታዳሽ የኃይል ኢንቨስትመንቶች፣ በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ የኔትወርክ መሠረተ-ልማቶች እና ኃይል ቆጣቢ አረንጓዴ የዳታ ማዕከላት አማካኝነት የካርቦን ልቀት ቅነሳን ላይ ውጤት ማስመዝገቡን አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ እንጦጦ (ቁስቋም ማዞሪያ) እንዲሁም በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች አረንጓዴ አሻራ ማሳረፊያ ፕሮግራም አከናውኗል፡፡

 የኢትዮቴሌኮም ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ፍሬሕይዎት ታምሩ እንዳስታወቁት ካምፓኒው ባለፉት ሰባት አመታት  በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ላይ በመሳተፍ በመላው ሀገሪቱ ከ4 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መትከል ተችሏል፡፡ ከተተከሉት ችግኞች ውስጥም  82 ነጥብ 7 በመቶ ያህሉ መጽደቃቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮቴሌኮም በዛሬው  ዕለት በተከታታይ ለስምንተኛ  አመት በሀገር አቀፍ ደረጃ “ለአረንጓዴ ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል 250 ሺህ ችግኞችን መትከሉን ዋና ስራ አስፈጻሟ ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ ለሚያለማቸው መሬቶች እና ችግኞች የእንክብካቤ ሥራዎች ከ159 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡንና  በቦታ ዝግጅት፣ በተከላ እና በእንክብካቤ ሂደት ውስጥ ከ4 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ አሰስረድተዋል፡፡

የአረንጓዴ ልማት  ኩባንያው በዘላቂነት  የሚያከናውናቸው ተግባራት አካል መሆኑን ጠቁመው  በታዳሽ የኃይል ኢንቨስትመንቶች፣ በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ የኔትወርክ መሠረተ-ልማቶች እና ኃይል ቆጣቢ አረንጓዴ የዳታ ማዕከላት አማካኝነት የካርቦን ልቀት ቅነሳን ማሳካት እንደቻለ አስታውቀዋል፡፡

ኩባንያው ከ9 በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያ ጣቢያዎች ከ481 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችን በማስተናገድ፣ ከ15.4 ሚሊዮን ኪሎግራም በላይ የካርቦን ልቀትን መከላከል እንደቻለ አስረድተዋል፡፡

 ኢትዮ ቴሌኮም በገጠር አካባቢዎች የፀሐይ ኃይል (ሶላር) አጠቃቀምን በማስፋፋት የሶላር አቅሙን ወደ 39 ነጥብ 7 ሜጋ ዋት ማሳደጉንና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

ተቋሙ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል፣ አካባቢን በመጠበቅ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ረገድ የማህበራዊና አካባቢያዊ ኃላፊነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories