በውል እርሻ የሚገዛ ምርት ከፍያው በኢትዮጵያ ምርት ገበያ (ECX) በኩል መፈጸም አለበት ተባለ

“ክፍያው በECX በኩል እንድትፈጽሙ መባሉ ግራ እጋብቶናል” ላኪዎች


በውል እርሻ የምትገዙትን ምርት ከፍያውን በECX በኩል እንድትፈጽሙ መባሉ ግራ እንዳጋባቸው  ላኪዎች ለኢትዮጵያ ቢዝነስ ቪው (EBV) ገለጹ፡፡

የውል እርሻ ላኪዎች ወደ ውጭ ከሚልኳቸው አንዱ አስመርተው የሚያገኙት ምርት  እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በዚህም በሚዛንና በጥራት ጉዳይ የኢትዮጵያ የምርት አገልግሎት እንደሚጎል የሚታወቅ ነው፡፡

 ከትላንት በስቲያ በተደረገው በላኪዎችና በንግድ ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በተደረገ የ2018 በጀት አመት አፈጻጸምና የ2019 እቅድ ውይይት ላይ ሚኒስቴሩ ላኪዎች በውል እርሻ የሚገዙትን ምርት ክፍያውን በኢትየዮጵያ ምርት ገበያ ስርአት ፈጽሙ ማለታቸውን ግርምት እንደፈጠረባቸው ነው ተሳታፊዎች የገለጹት፡፡

በመድረኩ የተሳተፉ ላኪዎች   በውል እርሻ ለሚገኝ የአርሻ ምርት አስመራቹ ቀደም ሲል ከፍያ የሚፈጸም መሆኑን አስታውሰው ሚኒስትሩ ቀሪውን በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ፈጽሙ ማለታቸው ግርንትን እንደፈጠረባቸው ነው የተናገሩት፡፡

በሌላ በኩል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በ2018 በጀት ዓመት ከጠቅላላ የወጪ ንግድ ከ11.2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

በ2019 በጀት ዓመት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ይበልጥ ለማሳደግ የ13.4 ቢሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ግብ የተቀመጠ መቀመጡን አስታውቀዋል፡፡

ዕቅዱን ለማሳካት  ምርቶችን በብዛት ከመላክ ባለፈ እሴት በመጨመርና ጥራትን በማረጋገጥ ተወዳዳሪ መሆን፤ ነባር ገበያዎችን ከማጠናከር ጎን ለጎን አዳዲስ ዓለም አቀፍ የገበያ መዳረሻዎችን መፈለግ፤ የወጪ ንግድን በዘመናዊ ዳታና ዲጂታል አሰራር በመደገፍ መምራት እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories