አዲሱ የቢሾፍቱ ግዙፉ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ዙሪያ የአሜሪካና ቻይና ፉክክር ዉስጥ አስገብቷል


ኢትዮጵያ በ12.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ልታስገነባው ያቀደችው አዲሱ የቢሾፍቱ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት በአሜሪካ እና በቻይና መካከል ከፍተኛ የጂኦፖለቲካዊ ፉክክር ውስጥ መክተቱ ተገለጸ። ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገነባው ይህ ግዙፍ ማዕከል የአፍሪካን ንግድና ጉዞ ለማቀላጠፍ ያለመ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮንትራት ጨረታውን ለመቆጣጠር ከባድ ውድድር እየተደረገበት ይገኛል።

የአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያከናወነ ባለው በዚህ ፕሮጀክት ላይ የመሠረተ ልማት ግንባታ ጨረታዎች አብዛኛዎቹ በቻይና መንግሥት ባለቤትነት የተያዙ ኩባንያዎች መሪነት እየተመሩ ይገኛሉ። ከእነዚህም መካከል የቻይና ሲቪል ምህንድስና ግንባታ ኮርፖሬሽን እና የቻይና መንገድና ድልድይ ኮርፖሬሽን ይገኙበታል፤ ይህም ቤጂንግ በኢትዮጵያ መሠረተ ልማት ዘርፍ ያላትን ጠንካራ የበላይነት አሳይቷል።

ምንም እንኳ የአሜሪካ ኮንስትራክሽን ኩባንያዎች በሲቪል ግንባታው ላይ ዝርዝር ውስጥ ባይካተቱም፣ ዋሽንግተን እንደ ቦይንግ እና ጄኔራል ኤሌክትሪክ ጂኢ ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች ለቀጣይ የቴክኖሎጂ እና የመሳሪያ አቅርቦት ውድድሮች እንዲያልፉ ግፊት እያደረገች ትገኛለች። የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ አጋርነት ለማጠናከር ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።


እንደ የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ከሆነ ፣ ይህ ውድድር የምስራቅ አፍሪካ መሠረተ ልማት ለአሜሪካና ቻይና ፉክክር አዲስ ግንባር መሆኑን የሚያሳይ ነዉ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከራሱ የበጀት አቅም 20 እስከ 30 በመቶ የሚሆነውን ፋይናንስ የሚሸፍን ሲሆን፣ ቀሪውን ገንዘብ ከአለም አቀፍ አበዳሪዎች ለማግኘት እየሰራ ይገኛል። የአፍሪካ ልማት ባንክ 500 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል የገባ ሲሆን፣ የአሜሪካ ልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን እና የጄፒ ሞርጋን ቼዝ ባንኮችም ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል።


ባለሙያዎች እንደሚሉት ቻይናውያን ኩባንያዎች በዋጋና በፈጣን አፈፃፀም የተሻሉ በመሆናቸው የሲቪል ግንባታ ኮንትራቶቹን ሊወስዱ ይችላሉ። በሌላ በኩል በአቪዮኒክስ፣ በደህንነት እና በዲጂታል መሠረተ ልማት ዘርፎች ምዕራባውያን ወይም የዓረብ ሀገራት አጋሮች ይመረጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ በ2030 ዓ.ም. እስከ 60 ሚሊዮን ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን ተጓዦች እና 4 ሚሊዮን ቶን ጭነት ማስተናገድ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል።seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories