በታሸገ ውሃ ከፍተኛ ዋጋ ጭማሪ ተደረገ

-ጭማሪው ተጋኗል ሲሉ ባለሞያዎች ተችተዋል

በኢትዮጵያ የውሃ ኢንደስትሪ ከትላንት ጀምሮ ከፍተኛ የዋጋ ክለሳ መደረጉን ለኢት ቢዝነስ ቪው የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለዘርፉ ቅርብ የሆኑ የመረጃ ምንጮች ለኢት ቢዝነስ ቪው እንደተናገሩት ከትላንት መስከረም 12 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የውሃ ዋጋ ጭማሪ ቀደም ሲል ከነበረው የ20 በመቶ ጭማሪ ነው፡፡

በ 7 ወር ውስጥ 3 ጊዜ ጭማሪ የተደረገ መሆኑን ያስታወሱት ምንጮች፤ ከ 150 ብር ተነስቶ አሁን ላይ 300 ብር ደርሷል ሲሉ አክለዋል፡፡

በቅርብ ጊዜ ማለትም ያለፈው ሰኔ ወር ላይ በተደረገው ጭማሪ 250 ብር ደርሶ አንደነበር አስታውሰው ከትላንት ጀምሮ ደግም 300 ብር ገብቷል ብለዋል።

ይሄ ፋብሪካዎች ለባለሱቆች የሚሸጡበት ዋጋ መሆኑ ነው የተገለፀው።

አንድ ፖክ የሁለት ሊትር ውሃ ዋጋ 300 ብር ነው ማለት አንዱ ጠርሙስ 50 ብር ነው ያሉት የመረጃ ምንጮች፡፡

ወደታች ሲወርድ ተጠቃሚዎች የሚገዙበት ዋጋ ከ 60 ብር እስከ 80 ብር ይደርሳል ማለት ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡


ለጭማሪ እንደ ምክንያት የተጠቀሰው የጥሬ ዕቃ ዋጋ ጭማሬ ቢሆንም፡፡ የጥሬ እቃ ዋጋ ይህን ያህል ግን አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለምሳሌ አሉ የዘርፉ ባለሞያዎች PET በመባል የሚታወቀው ጥሬ እቃ በኪሎ ከ 20-30 ነው የጨመረው ነገር ግን ባለሀብቶቹ ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው የተጋነነ ዋጋ በመጨመር ሌላ ስራቸውን እየደጎሙ ነው ሲሉ ነው ቅሬታቸውን የገለፁት፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ከ 100 በላይ የውሃ አምራቾች በተለያየ የአገሪቱ ክፍል እንደሚገኙ ይጠቀሳል፡፡

ከሰሞኑ በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ የሚታየው ሰላም እጦት እና ጦርነት ለውሃ ጥሬ እቃ መወደድ እንደ አብይ ምክንያት እየተጠቀሰ ነው፡፡
 

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories