ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ(ዶ/ር) የመንግስታቸውን ቀጥታ አቀጣይ አቅጣጫ አስመልክተው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተላለፈ የቀጥታ ስርጭት ንግግራቸው በሀገሪቷ በቀጣይ ትኩረት ያገኛሉ ያሉትን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስራዎችን አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትኩረት ያገኛሉ ብለው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል የህገ መንግስት ማሻሻያ እንደሚኖር፣በፖለቲካው ዘርፍ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርዎች ጋር ትብብርና ፉክክር እንደሚደረግና መንግስትም ለዚህ ዝግጁ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ሰላም ለማጽናት ውይይትና ይቅርታ ለማድረግ መንግስታቸው ዝግጁ እንደሆነ ጠቁመው ነፍጥ ላነሱ አካላትም የሰላም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ መንግስታቸው የሀገሪቱን ሰላም ለማጽናት ጠንካራ የደህንንት ቁጥጥርና ስምሪት ይኖራል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የመኖሪያ ቤት ችግርን ከስሩ ለመፍታት አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት መንግስታቸው እንደሚሰራ በሚሊየን ለሚቆጠሩ መኖሪያ ቤት ፈላጊዎችን ታሳቢ ያደረገ ንግግር አድርገዋል፡፡
ኢትዮጵያ ተዘግቶባት መኖር እንደማትችል የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ለማግኘት ይሰራል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡SECO


