መንግሥት የአዋሽ-ኮምቦልቻ የባቡር መስመር ግንባታን በራሱ አቅም መገንባት ጀመረ



​ የኢትዮጵያ መንግሥት የተቋረጠውን የአዋሽ–ኮምቦልቻ–ሃራ ገበያ የባቡር መስመር ጥገናና ግንባታ በራሱ አቅም ለማጠናቀቅ ሥራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ። ኮርፖሬሽኑ የራሱን የሰው ኃይል፣ ማሽነሪዎችና ቁሳቁሶችን በመጠቀም ፕሮጀክቱን እያንቀሳቀሰ ይገኛል።


​ይህ እርምጃ የተወሰደው ከቀድሞው ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ጋር በለንደን ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እየተካሄደ የሚገኘው የክርክር ሂደት ማጠቃለያ ላይ በደረሰበት ወቅት ነው።

 የኮርፖሬሽኑ የመሠረተ ልማት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ስለሺ ካሳ እንደገለጹት፣ የሀገር ውስጥ መሐንዲሶች ተቋራጩ ካቀረባቸው የካሳ ጥያቄዎች መካከል ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑትን ማሸነፍ ተችሏል።


​እስካሁን ባለው ሂደት ወደ 70 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የባቡር መስመር የተጠገነ ሲሆን፣ በቅርቡ የሙከራ ጉዞዎች ይጀምራሉ።

ኮርፖሬሽኑ የመጀመሪያውን ምዕራፍ እስከ ኮምቦልቻ ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ አቅዷል። እ.ኤ.አ. በ2015 በ1.7 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የተጀመረው ይህ 392 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ፕሮጀክት 12 ዋሻዎችንና 52 ድልድዮችን ያካተተ ሲሆን፣ ማዕከላዊውን የሀገሪቱን ክፍል ከሰሜን ክልሎች ጋር ለማገናኘት ታስቦ የተገነባ እንደሆነ ይታወቃል።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories