የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለፋይናንስ ዘርፉ ወሳኝ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ ያለውን ፋይዳ ዲጂታል የማንነት መረጃ ከሁሉም ባንኮች የደንበኞች ባንክ ሂሳብ ቁጥር ጋር የማጣመር (Harmonization) ስራን በዛሬው እለት በይፋ አስጀምሯል።
ይህ የመረጃ ሥርዓቶችን የማጣመር ስራ ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ገንዘብ ማስተላለፍ እንዲችሉ፣ በሀሰተኛ ሰነድ የእራሳቸውን ሂሳብ ሌሎች ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ፣ በቀላሉ የብድር አገልግሎትን ማግኘት እንዲችሉ፣ እና በአንድ ፋይዳ መታወቂያ የሁሉንም ባንክ ሂሳብ ለመጠቀም ያስችላል ተብሏል።
ባንኮች በዚህ መረጃ ጥምረት የደንበኞቻቸውን ትክክለኛ እና ወቅታዊ የሆነ መረጃን እንዲያገኙ፣ በሀሰተኛ ማንነት የሚከሰት የገንዘብ መጭበርበርን ከመከላከል ባለፈ ለፋይናንስ ሴክተር ዲጂታል ትግበራ ቁልፍ የዲጂታል መሰረተ ልማት ሆኖ ያገለግላል ነው የተባለው።
ይህን የባንክ ሂሳብ ቁጥር ከፋይዳ መረጃ ጋር ለማጣመር ደንበኞች ወደ ባንክ ቅርንጫፎቻቸው በአካል በመሔድ ወይም ኦንላይን (ባንኩ በሚያስቀምጠው አሰራር መሰረት) የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር (16 አሀዝ-FAN Number) በማቅረብ ማከናወን ሲቻል ደንበኞች እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መረጃ ጋር ማጣመር እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።Seco


