የአማራ ባንክ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት (ከሐምሌ 1 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018) በዋና ዋና የፋይናንስ አፈጻጸም ቁልፍ የስራ መስኮች ላይ ጠንካራና ከፍተኛ እድገት ማስመዝገቡና ወደ ትርፋማነት መመለሱን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው አስታውቀዋል:: ባንኩባለፉት አምስት ወራት ከታክስ በፊት የ1.15 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገብ እንደቻለ ነው የተገለጸው፡፡
የተገኘው ትርፍ በ2017 በጀት ዓመት ከተመዘገበው የ910.2 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱ ነው የተጠቆመው፡፡
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አምስት ወራት 3.55 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስመዝገብ እንደተቻለ ዋና ስራ አስፈፃመሚው ገልጸው ይህም የአማራ ባንክ ስትራቴጂካዊ እቅድ ትግበራ ጅምር ውጤታማነትና የአሰራር ቅልጥፍናን እያስመዘገበ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የትርፋማነት እድገት ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅቅ ከነበረበት ከ910.2 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ወጥቶ ወደ 1.15 ቢሊዮን ብር ትርፍ ከታክስ በፊት ማስመዝገብ አንደተቻለ ባንኩ ለቅዳሜ ገበያ በላከው መግለጫ ላይ መመልከት ተችሏል፡፡
የባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን እስከ ህዳር 2018 35.8 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ዕድገቱ 82 በመቶ ሲሆን ይህም በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ የ4.29 ቢሊዮን ብርብልጫ ማሳየት ችሏል፡፡
ባንኩ የ76.58 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ በመሰብሰብ የላቀ አፈጻጸም እንደሳየና ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ313 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል::
ባንኩ 52.3 ሚሊዮን ዶላር ወሳኝ የገቢና ሌሎች የውጭ ምንዛሪ ፍላጎቶችን ለመደገፍ ጥቅም ላ እንዳዋለ አስታውቋል፡፡
አማራ ባንክ ከተመሰረተ ጀምሮ ያቀረበው አጠቃላይ ብድርና የቅድሚያ ክፍያ አምና በተመሳሳይ ወቅት ከነበረበት በ53.8 በመቶ በማሳደግ ወደ 31.3 ቢሊዮን ብር ማበደር ችሏል፡
በህዳር 2017 ከነበረበት 12.9 በመቶ በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ያልተከፈለ/የተበላሽ/ ብድር(NPL) ጥምር ወደ 4.06 በመቶ ዝቅ ማለቱን አስታውቋል፡፡
የሞባይል ባንኪንግ ተመዝጋቢዎች ከ1 ሚሊዮን በላይ በመሆናቸው ባንኩ ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል፡፡
በዲጂታል ቻናል የሚደረግ ግብይት መጠን በዓመት በ108.5% ከፍ ሲል የዲጂታል ግብይቶች ከባንኩ አጠቃላይ የግብይት መጠን 27.6% እንደሚሸፍን ተነግሯል፡፡Seco


