የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገቢዎች ሚኒስቴርን እና የጉምሩክ ኮሚሽንን የ2018 በጀት ዓመት የአራት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ከገመገመ በኋላ፣ ገቢ አሰባሰባቸውን ለማሻሻል ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም እንዳለባቸው አሳስቧል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ እንዳስገነዘቡት፣ ቴክኖሎጂን መጠቀም የታክስ አጭበርባሪዎችንና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል እንዲሁም የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ ነው።
ሰብሳቢው ሁለቱ ተቋማት የገቢ አሰባሰብ ስርዓታቸውን በማጠናከር ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።Seco


