የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ከብሄራዊ ባንክ አመላካች ዋጋው ቅናሽ አሳይቶ ተጠናቋል

በኢቢቪ ዘጋቢ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በየ15 ቀኑ ማድረግ በጀመረው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የዛሬ 12ኛ ዙር ከቀደመው ዋጋ ምንም የሚባል ለውጥ እንዳላሳየ ታወቀ፡፡

በእለቱ ውጤታማ የተባለው አማካኝ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 154.77 ብር ሆኖ የተዘጋ ሲሆን ይህ መጠን ከቀዳሚው ጨረታ የ 37 ሳንቲም ወይም የዜሮ ነጥብ 2 (0.2) በመቶ ብቻ ጭማሪ የታየበት ነው፡፡

ከቀደሙት ልምዶች በመነሳት ይህ የጨረታ ውጤት ምንም የሚባል ለውጥ ከቀዳሚው የምንዛሬ መጠን አንፃር ያልታየበት ነው፡፡

በተመሳሳይ ይህ ጨረታ ብሄራዊ ባንክ በየቀኑ ከሚወጣው አመላካች የምንዛሬ ዋጋ የ19 ሳንቲም ቅናሽ ያሳየ ነው፡፡ ይህም ማለት ዛሬ ዶላር በጨረታ የገዙ 13 ባንኮች ዶላሩን የገዙት ከአመላካች ዋጋው የ ዜሮ ነጥብ 12 በመቶ ቅናሽ አግኝተው ነው፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ተደርጎ በነበረው 11ኛ ጨረታ የመግዣ ዋጋ 154.39 መሆኑ ይታወሳል ይህም የብር መግዛት አቅምን በ4.24 በመቶ ያዳከመ ነበር፡፡

ባለፉት ቀናት የብሄራዊ ባንክ አመላካች የምንዛሬ መጠን መለዋወጥ ሲያሳይ ቆይቶ ከ155 ብር በላይ ደርሶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የዛሬ ታህሳስ 7 ቀን ከሰአት አመላካች ዋጋ በዶላር 154.9 ብር ነው፡፡©SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories