የናይጄሪያ ናይራ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ አሳየ

የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችትም እያሽቆለቆለ መሆኑ ተገለጸ

የናይጄሪያ የገንዘብ ምንዛሬ ናይራ (Naira) በዚህ ሳምንት በአሜሪካ ዶላር ላይ ከፍተኛውን የዋጋ መውረድ ማስመዝገቡ ተገልጿል።

 የናይጄሪያ ማዕከላዊ ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በሳምንቱ መጨረሻ በይፋዊው የውጭ ምንዛሬ ገበያ አንድ ዶላር ወደ 1,464.49 ናይራ ከፍ ብሏል።

ይህ የዋጋ ለውጥ ካለፈው ታህሳስ 4 ቀን 2025 (እ.ኤ.አ) ወዲህ የታየ ከፍተኛው የቀን ተቀን የዋጋ መውረድ ሲሆን፣ በሳምንት ውስጥ ብቻ የናይራ ዋጋ በ12.67 ዶላር ቀንሷል። በተመሳሳይ በጥቁር ገበያ አንድ ዶላር በ1,500 ናይራ እየተመነዘረ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ሳምንት የ15 ናይራ ቅናሽ አሳይቷል።

ይህ የገንዘብ ዋጋ መውረድ ያጋጠመው የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ ባለበት ወቅት ነው። እንደ ዘገባው ከሆነ የናይጄሪያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት በ0.57 በመቶ ወይም በ0.20 ቢሊዮን ዶላር በመቀነስ 45.21 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህ በውጭ ምንዛሬ ክምችት ላይ የታየው ቅናሽ እና የናይራ የመግዛት አቅም መዳከም በሀገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ ተጨማሪ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ተገልጿል።@seco

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories