የብድር ስምምነትቱ በየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ተፈርሟል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ተወካይ እና የኮርፖሬት አገልግሎቶች ኤክስኪውቲቭ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ባንኩ የሁሉንም ህብረተሰብ ፍላጎት ማሟላት በሚያስችል መልኩ የብድር አገልግሎቱን በማሳደግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
በስምምነቱ መሠረት ባንኩ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች ቤት መሥሪያ የሚሆን የ27.8 ቢሊየን ብር ብድር እንደሚያቀርብ አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው አየር መንገዱ የሠራተኞቹን ችግር ለመፍታት ለ5ሺ ሠራተኞች መኖሪያ ቤት ግንባታ ወጪን ለመሸፈን ከንግድ ባንክ ጋር ለመሥራት ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡@seco


