ደቡብ አፍሪካ በጠቅላላ የሀብት መጠኗ አሁንም የአፍሪካ ቀዳሚዋ ባለጸጋ ሀገር ሆና መቀጠሏ ተገለጸ።
ሄንሊ ኤንድ ፓርትነርስ ያወጣውን መረጃ ዋቢ በማድረግ የወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ ሀገሪቱ በጠቅላላው የ410 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት (GDP) አላት። ይህም በአህጉሪቱ ካሉ ሀገራት ሁሉ ቀዳሚ ያደርጋታል።
ደቡብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ጥንካሬዋን ከሚያሳዩ መረጃዎች መካከል የባለጸጎቿ ቁጥር አንዱ ነው። በሀገሪቱ ውስጥ ከ41,000 በላይ ሚሊየነሮች እና ስምንት ቢሊየነሮች እንደሚገኙ ተመልክቷል።
ሀገሪቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያከናወነች ያለችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረትን ለመቅረፍ የምታደርገው ጥረት እና የመሠረተ ልማት ግንባታዎች የኢንቨስተሮችን እምነት መልሶ ለማግኘት እያገዟት ይገኛሉ።
ከዓለም ባንክ በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ የታገዙት የደቡብ አፍሪካ ሜትሮ ከተሞች እና ጠንካራው የፋይናንስ ዘርፍ፣ ሀገሪቱ በአህጉሪቱ ያላትን የኢኮኖሚ የበላይነት አጠናክራ እንድትቀጥል አቢይ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸው ተዘግቧል።@seco


