ቻይና አሜሪካ በድሮን ኩባንያዎቿ ላይ የጣለችውን እገዳ አጥብቃ ተቃወመች

የአሜሪካ መንግሥት የቻይና ድሮን አምራቾችን በሀገሪቱ የደህንነት ስጋት ዝርዝር ውስጥ ማካተቱን ተከትሎ፣ የቻይና ንግድ ሚኒስቴር ድርጊቱ “የተሳሳተ አሰራር” ነው ሲል ወቅሷል።

ቤጂንግ የኩባንያዎቿን መብት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ እንደምትወስድም ዝታለች።

የአሜሪካው የፌዴራል ኮሙኒኬሽን ኮሚሽን (FCC) ባሳለፍነው ሰኞ ባወጣው መግለጫ፣ ታዋቂዎቹን የቻይና ድሮን አምራቾች DJI እና Autel ጨምሮ ሁሉንም በውጭ ሀገር የተሰሩ የድሮን ሲስተሞችና መለዋወጫዎችን በ “Covered List” ወይም የታገዱ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ዝርዝር ውስጥ አካትቷል።

ኮሚሽኑ ለዚህ ውሳኔ በምክንያትነት የጠቀሰው እነዚህ የድሮን ውጤቶች ለአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት “ተቀባይነት የሌለው ስጋት” ይፈጥራሉ የሚል ሲሆን፣ በዚህም መሰረት አዳዲስ የድሮን አይነቶች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ወይም ለሽያጭ እንዳይቀርቡ ፍቃድ መከልከሉን አስታውቋል።

የቻይና ንግድ ሚኒስቴር በበኩሉ አሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት የሚለውን ጽንሰ-ሀሳብ ያለአግባብ እየተጠቀመችበት ነው በማለት ይህንን “የተሳሳተ አካሄድ” በአስቸኳይ እንድታቆም አሳስቧል።

በተጨማሪም ቻይና የኩባንያዎቿን ህጋዊ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች።

ይህ አዲስ እገዳ በአሜሪካ ገበያ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸውን እንደ DJI ያሉ ኩባንያዎችን ክፉኛ የሚጎዳ ሲሆን፣ በሁለቱ የዓለም ልዕለ ኃያላን ሀገራት መካከል ያለውን የቴክኖሎጂና የንግድ ጦርነት ይበልጥ ያባብሰዋል ተብሎ ተሰግቷል።@seco

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories