ጥራጥሬ እና ቅባት እህሎች የኤክክፖርት የዋጋ ማሻሻያ ቢደረግም ላኪዎች ምርቶቹን በክምችት ይዘዋል ተባለ

መጋዘኖችን በመፈተሽ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር  አስጠንቅቋል

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች  ከኢትዮጵያ ጥራጥሬ እና ቅባት እህሎች ላኪዎች ማህበር የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ጋር ባደረገው ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው ባለፉት ወራት የጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች ምርት የኤክስፖርት አፈፃፀም እጅግ ዝቅተኛ እንደሆነ  ነው የተነገረው ፡፡

እንደሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገለጻ በሃገር ውስጥ ከፍተኛ የምርት ክምችት ቢኖርም ምርቱን  ላኪዎች በክምችት ይዘውታል፡፡

በውይይቱ ላይ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ  የኤክክፖርት የዋጋ ማሻሻያ መደረጉን ያስታወሰ ሲሆን ላኪዎች በክምችት የያዙትን ምርቶች በፍጥነት እንዲያወጡ እስስቧል፡፡

ላኪዎች ምርቶቹን በፍጥነት ካላወጡ ፍተሻ በማካሄድ መጋዘኖች እስከማሸግ እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት በፀደቀው ደንብ መሰረት ምርቱን መልሶ በምርት ገበያ እስከመሸጥ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories