ህንድ ጃፓንን ገለበጠች
በከፍተኛ ፍጥት አዳጊ ከሚባሉ ኢኮኖሚዎች አንደኛው የህንድ ኢኮኖሚ በተጠናቀቀው 2025 በአለም ደረጃ 4ኛ ቦታ ላይ መቀመጡን ህንድ አስታወቀች።
በኢኮኖሚ ደረጃ ጃፓንን ገልብጠናል ያለችው። የ3ኛ ደረጃን ባጠረ ጊዜ እናሳካለን ስትል አክላለች።
እንደሚባለው ከሆነ ግፋ ቢል በቀጣይ 3 አመታት ህንድ ጀርመንን በመብለጥ 3ኛዋ ግዙፍ የአለማችን ኢኮኖሚ መሆኗ አይቀርም።
የኢኮኖሚ ገለፃ ፓለቲካው የጎላ መሆኑን የሚናገሩት ባለሞያዎች የህንድ ደረጃ ማሻሻል ዜጎቿ ከጃፓን አቻዎቻቸው የኑሮ ደረጃ እጅግ ዝቅ ያለ መሆኑን እንዳያዘነጋ ሲሉ አክለዋል።
በነገራችን ላይ IMF የህንድ ኢኮኖሚ በ2026 ጃፓንን እንደሚበልጥ ተንብዮ ነበር።@seco


