ዳሸን ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት (2017) ከፍተኛ የፋይናንስ አፈጻጸም በማስመዝገብ አጠቃላይ ገቢውን 31.4 ቢሊዮን ያደረሰ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ34% ከፍተኛ ጭማሪ እንዳገኘ ነው ያስታወቀው።
ባንኩ በበጀት ዓመቱ ጠቅላላ ሃብቱን ከ254 ቢሊዮን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን ይህም በቀደመው የበጀት ዓመት ከነበረው 183.7 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር የ38.5 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡ ነው የተገለጸው፡፡
የባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 202.2 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ38.7% ጉልህ ጭማሪ አሳይቷል። ከጠቅላላው የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ የዳሸን ባንክ ወለድ ነፃ አገልግሎት (ሸሪክ) የ15.8 ቢሊዮን ብር አስተዋጽኦ ማድረጉ ተነግሯል።
ባንኩ በበጀት ዓመቱ 6.7 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን፣ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ5.1% ጭማሪ አሳይቷል።
በውጭ ምንዛሪ ግኝት ረገድም 1.12 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር አግኝቷል።
የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን፣ ዳሸን ባንክ በኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውስጥ መሪነቱን ያስመሰከረበትን የዳሸን ሱፐር አፕ መተግበሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለባንክ ኢንዱስትሪው ያበረከተበት ዓመት እንደነበር ተናግረዋል፡፡
የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ በበኩላቸው፣ በበጀት ዓመቱ የባንኩ ባለአክሲዮኖች ላሳዩት ያልተቋረጠ ድጋፍ፤ ደንበኞች ለጣሉት እምነት፤ እንዲሁም የባንኩ ሰራተኞች የላቀ አገልግሎት በመስጠት ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።@seco


