በቻይና ፉጂያን ግዛት የሚገኘው የዣንግዡ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ፣ በዓለም ትልቁ የሆነውን የ”ኋሎንግ ዋን” ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ማጠናቀቁን ይፋ አደረገ።
የጣቢያው ሁለተኛው ክፍል ለ168 ሰዓታት ያህል ሙሉ በሙሉ በከፍተኛ ኃይል ሲሞከር ቆይቶ ሐሙስ ዕለት በይፋ ወደ ሥራ በመግባቱ፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ በስኬት መጠናቀቁ ተገልጿል።
ይህ ማመንጫ ጣቢያ በአጠቃላይ ስድስት ክፍሎች እንዲኖሩት ታቅዶ የተገነባ ሲሆን፣ አሁን ሥራ የጀመሩት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ክፍሎች ብቻ በዓመት ከ10 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም አላቸው።
“ኋሎንግ ዋን” ሙሉ በሙሉ በቻይናውያን ቴክኖሎጂ የበለፀገ የሦስተኛ ትውልድ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ሲሆን፣ ቻይና በዘርፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን መሪነት የሚያሳይ ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል።
ስድስቱም ክፍሎች ግንባታቸው ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገቡ፣ በዓመት 60 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት ንጹህ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ ፕሮጀክት ከድንጋይ ከሰል የሚገኝን ኃይል በመተካት በየዓመቱ የሚለቀቀውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን በ8.16 ሚሊዮን ቶን እንደሚቀንስ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ቻይና ወደ ንጹህ የኃይል ምንጭ የምታደርገውን ሽግግር በእጅጉ ያግዛል ተብሏል።@SECO


