ግዙፉ የፈረንሳይ ሱፐር ማርኬት አስተዳዳሪ ካርፉር ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኩዊንስ ሱፐርማርኬት ጋር ይፋዊ የቢዝነስ ቅንጅት/ፍራንቻይዝ ለማድረግ ተስማማ

በበርካታ የአለም ክፍሎች በተመጣጣኝ ዋጋ ሸቀጥ በማቅረብ የሚታወቀው ካርፉር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባ ሲገለፅ ቆይቷል።

ኢትዮዽያ ለዘመናት ለሌሎች ተከልክሎ የነበሩ የንግድ ዘርፎችን እያላላች እንደሆነ ይታወቃል።

ከዚህም መካከል የችርቻሮ ንግድ አንዱ ነው።

ምንም እንኳን በከፍተኛ ደረጃ ለሚሰራ የችርቻሮ ንግድ የውጭ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ህጉ ከ3 አመት በፊት ቢስተካከልም ይህ ነው የሚባል ኩባንያ እስካሁን ስራ በይፋ አልጀመረም።

ኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በካርፉር ላይ የ25 በመቶ ድርሻ ባለው እና በአረቡ አለም፣ እስያ እና አፍሪካ ሱፐር ማርኬቶቹን በማስተዳደር መብት ባለው የተባበሩት አረብ ኤምሬቱ መጅድ አል ፉታይም አማካኝነት እንደሚገባ ነው የሚጠበቀው።

ሚድሮክ እንዳለው የንግድ ትብብር ስምምነቱ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ፍራንቻይዝ (franchise) ለኢትዮጵያ ገበያ የሚያስተዋውቅ ሲሆን በኩባንያው የዕድገት ጉዞ ላይ ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት ነው።

“ጠንካራ የሀገር ውስጥ አቅምን ከዓለም አቀፍ የችርቻሮ ንግድ ልምድ ጋር በማቀናጀት፣ የሀገር ውስጥ ሸማቾችን በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል እንዲሁም የኢትዮጵያ ምርቶች ዓለም አቀፍ ደረጃን አሟልተው ለዓለም ገበያ እንዲቀርቡ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ያስችለናል፣” ሲል ነው ያከለው።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories