የኢትዮጵያ የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮቦንድ ዋጋ በለንደን የአክሲዮን ገበያ ላይ ጭማሪ አሳየ

​ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2014 ዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ያወጣችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮቦንድ ዋጋ፣  በለንደን የአክሲዮን ገበያ ላይ በአሜሪካ ዶላር የ3 ሳንቲም ጭማሪ ማሳየቱን ብሉምበርግ ዘግቧል። ይህ የዋጋ ጭማሪ የተመዘገበው የኢትዮጵያ መንግሥት ዩሮቦንዱን ለማሸጋሸግ ከቦንዱ ያዥ ኢንቨስተሮች ኮሚቴ ጋር ባለፈው ሳምንት በመርህ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሱን ተከትሎ ነው።

​የዩሮቦንዱ ዋጋ መጨመር ኢንቨስተሮች ለቦንዱ ያላቸው ፍላጎት ማደጉን የሚያመለክት ሲሆን፣ በአንጻሩ ኢትዮጵያ ለቦንዱ የምትከፍለው የወለድ መጠን መቀነሱን ያሳያል። የኢትዮጵያ መንግሥት የዩሮቦንዱን 45 በመቶ የያዙ ኢንቨስተሮችን ከወከለው ኮሚቴ ጋር ስምምነት የደረሰው፣ ቦንድ ያዦቹ በዩሮቦንዱ ዋጋ ላይ የ15 በመቶ ቅናሽ (Haircut) እንዲያደርጉ መንግሥት ባቀረበው ሃሳብ መሠረት መሆኑ በዘገባው ተመልክቷል።

​በሌላ በኩል፣ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ይህ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በቦንድ ያዦች መካከል የተደረሰው ስምምነት፣ ተቋሙ ለኢትዮጵያ ከፈቀደው የ3.6 ቢሊዮን ዶላር የብድር ፕሮግራም ዓላማ ጋር የሚጣጣም መሆን አለመሆኑን በቀጣይ ቀናት እንደሚገመግም ሮይተርስ ዘግቧል።@SECO

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories