በደቡብ አፍሪካ የነዳጅ ዋጋ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛው የተባለለትን ዋጋ ሊያስመዘግብ መሆኑ ተገለጸ። ለዚህ የዋጋ ቅናሽ ዋነኛ ምክንያቶቹ የዓለም አቀፍ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ መቀነስ እና የደቡብ አፍሪካ መገበያያ ገንዘብ “ራንድ” ከአሜሪካ ዶላር አንጻር መጠናከር መሆናቸው ተመልክቷል።
እንደ ሀገሪቱ የማዕድንና የፔትሮሊየም ሀብት ሚኒስቴር መረጃ፣ እኤአ ከጥር 7 ጀምሮ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ማዕከል በሆነችው ጋውቴንግ የ95-ኦክቴን ቤንዚን የችርቻሮ ዋጋ በ3 በመቶ ቅናሽ በማሳየት በአንድ ሊትር 20.75 ራንድ ($1.26) ይሆናል።
በተመሳሳይ የዲዝል ዋጋ በ7 በመቶ ከፍተኛ ቅናሽ የሚያሳይ ሲሆን፣ ይህም ለትራንስፖርት ዘርፉና ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ትልቅ እፎይታን እንደሚሰጥ ብሉምበርግ ዘግቧል።
ደቡብ አፍሪካ የምትጠቀመውን ድፍድፍ ነዳጅ ሙሉ በሙሉ ከውጭ የምታስገባ በመሆኑ፣ የሀገሪቱ ገንዘብ “ራንድ” በታህሳስ ወር ላይ ከአሜሪካ ዶላር አንጻር የ3 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ለነዳጅ ዋጋው መቀነስ ቀጥተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል።@SECO


