ኬንያ የአሜሪካ ኩባንያዎችን ከዝቅተኛው የድርጅት ግብር ነፃ አደረገች

የኬንያ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ግዙፍ የአሜሪካ ኩባንያዎችን “ከዝቅተኛ የድርጅት ግብር” ነፃ የሚያደርግ ስምምነት መፈረሙ ተገለጠ።

ይህ ውሳኔ የኬንያ ገቢዎች ባለሥልጣን አንደ ጎግል፣ ሜታ፣ አማዞን እና ኔትፍሊክስ ካሉ የቴክኖሎጂ ግዙፍ ተቋማት ቢሊዮን የሚቆጠር ተጨማሪ ታክስ ለመሰብሰብ የነበረውን ዕቅድ ክፉኛ ጎድቶታል።

በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ መካከለኛነት የተደረሰው ይህ ስምምነት፣ የአሜሪካ ኩባንያዎች በመላው ዓለም በሚያከናውኑት የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ግብር የመጣሉ ሉዓላዊ መብት የአሜሪካ ብቻ መሆኑን የሚደነግግ ነው።

ይህ በኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ድርጅት ማዕቀፍ የተመቻቸው ስምምነት፣ ኬንያ በ2024 ባጸደቀችው የታክስ ሕግ መሠረት ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ቢያንስ 15 በመቶ የድርጅት ግብር እንዲከፍሉ ያስቀመጠችውን ድንጋጌ የሚቃረን ነው።

የታዋቂው የጂኦ-ፖለቲካ ኢኮኖሚስት አሊ-ካን ሳቹ አስተያየት እንደሚያሳየው፣ ውሳኔው የአሜሪካ ኩባንያዎች በየትኛውም የዓለም ክፍል ቢሰሩም የሚገዙት በአሜሪካ የታክስ ሥርዓት ብቻ መሆኑን የሚያረጋግጥና ለኬንያ የታክስ ገቢ ትልቅ ኪሳራ የሚያስከትል ነው።

ኬንያ ይህንን ታክስ ለመሰብሰብ ቀጠሮ ይዛ የነበረ ቢሆንም፣ አዲሱ ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት ግን የኬንያን የገቢ ምንጭ በማጥበብ የአሜሪካን ኩባንያዎችና ሠራተኞችን ከውጭ አገር የታክስ ጣልቃ ገብነት የሚከላከል ሆኗል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories