በኢቢቪ ዘጋቢ
በአለም ላይ በድመት ወዳጆች ምልከታ፤ በመጠን፣ በቁመት፣ በፀጉር ወይ በከለር አለያ በሌላ መስፈርት ከ45 እስከ 70 የሚጠጉ የድመት ዝርያዎች አሉ።
ከነዚህ መካከል ጨዋታ ወዳድዋ እና ከባለቤቷ ስር ስር ትላለች እየተባለች በድመት አድናቂዎች የምትገለፀው እና የውሻ ባህሪ ነው ያላት የምትባለው ድመት የዝርያ መለያዋ ከኢትዮጵያ ጋር የሚገናኝ ነው።
ድመቲቱ አፈጣሯ ወይም የዘር መነሻዋ ከኢትዮጵያ ስለሆነ አይደለም ‘የአቢሲኒያ ድመት’ የሚል የዝርያ መጠሪያ ያገኘችው።
ነገሩ ሌላ ነው!
የዘርፉ አጥኚዎች እንደሚሉት አቢሲኒያ የተሰኘችው የድመት ዝርያ መነሻዋ ከደቡብ ምስራቅ እስያ እና በህንድ ውቅያኖስ ጠረፋማ ቦታ እንደሆነ ነው የሚጠቅሱት።
ታዲያ ከኢትዮጵያ ጋር ምን አገናኛት?
እንደሚገመተው ከሆነ ተጓዦች ከኮልኮታ ወደ ኢትዮጵያ ሳያመጣት አልቀረም።
ይሁንና ለአለም በአውሮፓ በኩል የተዋወቀችው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ነው።
የጀነራል ሮበርት ናፒየር ጦር ወደ መቅደላ ሲመጣ ለጦርነት ብቻ አለንበረም።
በ1860 የገጠመውን ድል ተከትሎ በሁሉም መስክ ከፍተኛ ዝርፊያ እንደፈፀመ የሚታወስ ነው።
ከዚህም መካከል ወደ እንግሊዝ በጀነራሉ የተወሰደችው ድመት ትገኝበታለች።
እንግዲህ ከዛን ጊዜ አንስቶ ይህች ድመት ዝርያዋ አቢሲኒያ በመባል ነው የሚለየው።


