ለትግራይ ክልል ከተመደበው በጀት ውስጥ እየተላከ ያለው አንድ ሶስተኛው ብቻ ነው ተባለ

በክልሉ ያለውን የበጀት እጥረት ለመቅረፍ  በሲሚንቶ፣ በመጠጦችና በታሸጉ ውሃዎች ላይ አዲስ የዋጋ ጭማሪ ተጥሏል

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እያጋጠመው ያለውን የበጀት እጥረት ለመቅረፍ እና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለማስቀጠል ሲል በተለያዩ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ሀብት ለማሰባሰብ መወሰኑን አስታወቀ።

የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር አብርሀም ተከስተ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ፣ ከፌዴራል መንግስት የሚላከው በጀት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ገልጸዋል።

 እንደ ሰብሳቢው ገለፃ፣ ከጥቅምት ወር ወዲህ ለክልሉ ከተመደበው በጀት ውስጥ እየተላከ ያለው አንድ ሶስተኛው ብቻ በመሆኑ፣ አስተዳደሩ በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ለመርዳትና የመንግስት ስራዎችን ለማስኬድ በገንዘብ እጥረት ተፈትኗል።

ይህንን ችግር ለመፍታት የወጣው አዲስ ደንብ በንግድ ምርቶች ላይ የሚከተሉትን የዋጋ ጭማሪዎች ደንግጓል፦

 * በመጠጦች ላይ፦ በአንድ ቢራ ላይ 3 ብር፣ በአንድ ጠርሙስ አረቄ ላይ 10 ብር፣ በወይን ላይ 20 ብር እንዲሁም በአንድ ጠርሙስ ውስኪ ላይ 200 ብር ጭማሪ ተደርጓል።

 * በውሃ እና ለስላሳ፦ በአንድ ደርዘን የታሸገ ውሃ ላይ 12 ብር፣ በለስላሳና አምቦ ውሃ ላይ ደግሞ 1 ብር ተጨምሯል።

 * በግንባታ ዕቃዎች፦ በአንድ ኩንታል ሲሚንቶ ላይ 100 ብር ጭማሪ ተደርጓል።

ይህ የሀብት ማሰባሰብ ሂደት በ13 ባንኮች በተከፈተ ሂሳብ እና በሰባት ንዑስ ኮሚቴዎች አማካኝነት የሚመራ ሲሆን፣ አሰባሰቡም ኮሚቴው በሚያሳትመው ልዩ ደረሰኝ ብቻ እንደሚከናወን ተገልጿል።

የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ምህረት በየነ እንደተናገሩት፣ ከዚህ የሚገኘው ገቢ ለመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ፣ ለፍትህና ፀጥታ አካላት ስራ ማስኬጃ እንዲሁም ለተፈናቃዮች ድጋፍ የሚውል ይሆናል ተብሏል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories