በኢቢቪ ዘጋቢ
ከደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ አካባቢ በሚወጡ መረጃዎች መሰረት ሁለት ቱርካውያንን ቱሪስቶች እና አሽከርካሪዎች በደረሰባቸው ጥቃት መገደላቸው ትላመንት ምሽት በክልሉ መንግስት የወጡ መረጃዎችን ጠቅሶ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ከቱሪስቶቹ መካከል ኤርዶጋን አክቡላክ የተባሉ የማእድን ኩባንያ ባለቤት እንደሚገኙበት ተርኪሽ ሚኒት የተሰኘ የዜና ተቋም ገልጿል፡፡
የክልሉ መንግስት ግለሰቦች በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ አርብቶ አደሮች መገደላቸውን ገልፆ አጥቂዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ጥቃቱ የተፈፀመው ሰኞ ጠዋት ከአዲስ አበባ 330 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ሱሪ ወረዳ መሆኑ ነው የታወቀው፡፡©SECO

