አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ75 አገራት ዜጎች የስደተኝነት ቪዛ ሂደት አገደች
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያ እና ኤርትራን ጨምሮ ከ75 አገራት ለሚመጡ ሰዎች የስደተኝነት ቪዛ የሚሰጥበትን ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ አግዷል።
ውሳኔው የተላለፈው በመንግሥት ድጋፍ የሚኖሩ ስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ እንደሆነ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያስታወቀ ሲሆን ውሳኔውም ከጥር 13/2018 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ነው የተገለጸው፡፡
ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆነው ውሳኔ፤ 75 አገራትን ያካተተ ሲሆን እንደሚመለከት ተገልጿል። የዜና ወኪሉ አሶሺየትድ ፕሬስ ያወጣው አገራት ዝርዝር እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ከእነዚህ አገራት አንዷ ነች። ከኢትዮጵያ ጎረቤት አገራት መካከል ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን እገዳ ከተጣለባቸው አገራት መካከል ተካትተዋል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ዩጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎም ውሳኔው የሚመለከታቸው የምስራቅ አፍሪካ አገራት ናቸው። ሩሲያ፣ ኢራን፣ ግብጽ፣ ሊቢያ፣ የመን እና ሶርያም ከ75 አገራት መካከል ተጠቅሰዋል።
በአዲሱ ውሳኔ መሰረት ከእነዚህ አገራት የሚመጡ ሰዎች የሚያቀርቡት ስደተኝነት ቪዛ ተቀባይነት አይኖረውም። ይህ እገዳ የተላለፈው በጊዜያዊነት እንደሆነ ቢጠቆምም ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ አልተገለጸም።@SECO


