የዓለም ኢኮኖሚ ለንግድ ጫናዎች የማይበገሩ መሆኑን አይ ኤም ኤፍ (IMF) አስታወቀ

የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂቫ፣ የዓለም ኢኮኖሚ ለንግድ ጫናዎችና ለተለያዩ ቀውሶች አስገራሚ የመቋቋም አቅም እያሳየ መሆኑን ገለጹ።

 ዳይሬክተሯ በዩክሬን ኪየቭ ሆነው ለሮይተርስ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ፣ ድርጅታቸው በቀጣዩ ሳምንት (ጥር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ የሚያደርገው የዓለም ኢኮኖሚ ትንበያ፣ ኢኮኖሚው ከንግድ መስተጓጎሎች በላይ ጠንካራ መሆኑን እንደሚያሳይ አመልክተዋል።

እንደ ጆርጂቫ ገለጻ፣ ምንም እንኳ አሜሪካ ባለፈው ዓመት በተለያዩ አገራት ላይ ከፍተኛ የታሪፍ ጫናዎችን ብታሳድርም፣ የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት ግን አልተገታም። አይ ኤም ኤፍ በነሐሴ ወር 2017 (ጥቅምት 2024) የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያውን ለ2025 ወደ 3.2% ከፍ አድርጎ የነበረ ሲሆን፣ አሁንም ይፋ የሚደረገው ጥር 11 ቀን 2018 ዓ.ም የሚወጣው ሪፖርት ተመሳሳይ ጥንካሬን እንደሚያንጸባርቅ ይጠበቃል።

ዳይሬክተሯ አክለውም፣ ምንም እንኳ አፈጻጸሙ ጥሩ ቢሆንም አሁንም ስጋቶች እንዳሉ አስጠንቅቀዋል። ከእነዚህም መካከል፦የጂኦፖለቲካ ውጥረቶች ፣ የቴክኖሎጂ ለውጥ እና የመጠባበቂያ ገንዘብ እጥረት አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories