ቻይና የአገሯ ኩባንያዎች የአሜሪካና የእስራኤል የሳይበር ደኅንነት ሶፍትዌሮችን መጠቀም እንዲያቆሙ አዘዘች

የቻይና መንግሥት በአገር ውስጥ የሚገኙ ኩባንያዎች ከአሥር በላይ የሚሆኑ የአሜሪካና የእስራኤል ተቋማት ያመረቷቸውን የሳይበር ደኅንነት ሶፍትዌሮችን መጠቀም እንዲያቆሙ አስቸኳይ መመሪያ ማስተላለፉ ተገለጠ።

ቤጂንግ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈችው “ብሔራዊ ደኅንነትን ለመጠበቅ” በሚል ምክንያት ሲሆን፣ ይህም በዋሽንግተን እና በቤጂንግ መካከል ያለውን የቴክኖሎጂ የበላይነት ፉክክር ይበልጥ እንደሚያፋፍመው ተነግሯል።

በዕገዳው የተካተቱ ዋና ዋና ኩባንያዎች

በመመሪያው መሠረት አገልግሎታቸው እንዲቆም የተጠየቁት ኩባንያዎች ቪኤምዌር ፣ ፓሎ አልቶ ኔትወርክስ ፣ ፎርቲኔት፣ ክራውድ ስትራይክ፣ ማንዲያንት እና ማክአፊ ይገኙበታል። በተጨማሪም የእስራኤል ኩባንያዎች፦ ቼክ ፖይንት፣ ሳይበር አርክ ፣ ኦርካ ሴኪውሪቲ እና ካቶ ኔትወርክስ ተካተዋል።

የቻይና ባለሥልጣናት እነዚህ ሶፍትዌሮች ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን ሰብስበው ወደ ውጭ አገር ሊያስተላልፉ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።

እንደ ዘገባዎቹ ከሆነ፣ አዲሱ የቻይና የሳይበር ደኅንነት ሕግ ማሻሻያ ከነገ በስቲያ ጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን፣ መመሪያውን የማይከተሉ ኩባንያዎች እስከ 10 ሚሊዮን ዩዋን (1.4 ሚሊዮን ዶላር) ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

ይህ እርምጃ ቻይና የምዕራባውያንን ቴክኖሎጂ በአገር ውስጥ ምርቶች (እንደ 360 Security እና Neusoft ባሉ) ለመተካት የምታደርገው ሰፋ ያለ ጥረት አካል ነው።

ውሳኔው በተለይም በቻይና ውስጥ ቅርንጫፍ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ለከፍተኛ የሥራ መስተጓጎል እና ለተጨማሪ ወጪ እንደሚዳርጋቸው የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እየተነበዩ ይገኛሉ።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories