የሱዳን የእንስሳት ላኪዎችና የመርከብ ኩባንያዎች አዲስ የተጣለውን ታክስ በመቃወም ሥራ አቆሙ

የሱዳን የእንስሳት ላኪዎችና የጭነት መርከብ ኩባንያዎች በመንግሥት የተጣለባቸውን አዲስ ታክስ በመቃወም ወደ ውጭ አገር የሚደረጉ የእንስሳት የዉጪ ንግድ እንቅስቃሴዎችን ሙሉ በሙሉ ማቆማቸውን አስታወቁ።

ላኪዎቹ ሥራ ያቆሙት በፖርት ሱዳን የሚገኘው “የሱዳን-ቻይና ወደብ አገልግሎት ኩባንያ” ከጥር 2026 ጀምሮ በእንስሳት ኤክስፖርት አገልግሎት ላይ የ17 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) በቅድሚያ እንዲከፈል መመሪያ ማውጣቱን ተከትሎ ነው።

የዘርፉ ተዋንያን ይህ አዲስ ታክስ ቀድሞውኑ በጦርነት ለደከመው የአገሪቱ ብሔራዊ ኢኮኖሚ ትልቅ ስጋት መሆኑን ገልጸው፣ ኩባንያው ምንም ዓይነት ተጨባጭ አገልግሎት ሳይሰጥ የራሱን የታክስ ግዴታ በላኪዎች ላይ መጫኑ “ሕገ-ወጥ ብዝበዛ” ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

ይህ የሥራ ማቆም አድማ ሱዳን በዋናነት የእንስሳት ምርቶቿን በስፋት ለምትልክላቸው እንደ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ኳታር እና ኦማን ላሉ የባሕረ ሰላጤው አገራት የምግብ አቅርቦት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ተሰግቷል።

የሱዳን የእንስሳት ላኪዎች ማኅበር እንደገለፀው ፣ እንዲህ ያሉ መሠረተ ቢስ ክፍያዎችና የታክስ ጫናዎች ሕጋዊውን ንግድ በማዳከም የእንስሳት ኮንትሮባንድ እንዲስፋፋ በር የሚከፍቱ ናቸው።

ቀውሱን በውይይት ለመፍታት በመንግሥትና በግል ዘርፉ መካከል በፖርት ሱዳን አስቸኳይ ስብሰባ የተጠራ ሲሆን፣ ስምምነት ላይ ካልተደረሰ ግን በሱዳን የውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚደርስ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories