የአውሮፓ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሲገቡ የሚገጥሟቸውን የመረጃ አቅርቦት ችግሮች ይቀርፋል የተባለ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የልህቀት ማዕከል ተከፈተ
በኢትዮጵያ የአውሮፓ የንግድ ምክር ቤት አዲስ ቢሮ እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የልህቀት ማዕከል ምቃት ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር ) የቢሮ እና የልህቀት ማዕከከሉ መከፈት የአውሮፓ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሲገቡ የሚገጥሟቸውን የመረጃ አቅርቦት ችግሮች በመቅረፍ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ጥራት ያለው የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ተዓማኒነት ያለው የማማከር አገልግሎት አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ ቀደም ሲል ብቃታቸው ባልተረጋገጡ አካላት የሚሰጡ የተሳሳቱ መረጃዎች ባለሀብቶችን ለስህተት ሲዳርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም ችግሩን ለመቅረፍ ኮሚሽኑ በኢንቨስትመንት ማማከር አገልግሎት ዘርፉ ላይ ጥብቅ የብቃት መስፈርትና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሥርዓት ለመዘርጋት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።@SECO


