ኢትዮ ቴሌኮም እና ሶምኬብል በአህጉራዊ የዲጂታል ትብብር እና ስትራቴጂያዊ አጋርነት መመስረት ያስችላል የተባለ ውይይት አካሄዱ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ከሶምኬብል (Somcable) ሊቀመንበር መሐመድ ሰይድ ጉኡዲ እና ዋና ስራ አስፈጻሚ መሐመድ ኢብራሂም አህመድ ጋር በዓለም አቀፍ ዲጂታል እና ቴሌኮሙኒኬሽን ቢዝነስ ዘርፍ ድንበር ተሻጋሪ አጋርነት ለመመስረት ስትራቴጂያዊ ውይይት ነው ያካሄዱ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ኩባንው ድንበር ተሻጋሪ የዲጂታል መፍትሄዎችን ለማስፋፋት ያለውን ቁርጠኝነት ጠቁመው “ትብብር ለዲጂታል ዕድገት ወሳኝ ነው፤ ይህ አጋርነት የጋራ እሴት ለመፍጠርና በአፍሪካ የዲጂታል አቅምን ለማጎልበት ተሞክሯችንን እንድንጋራ ያስችለናል” ብለዋል፡፡

የሶምኬብል ሊቀመንበር “ከአፍሪካ ቀዳሚ ኦፕሬተሮች አንዱ ከሆነው ኩባንያ ጋር አጋር በመሆናችን ታላቅ ኩራት ይሰማናል” ያሉ ሲሆን የሶምኬብል ዋና ሥራ አስፈጻሚ በበኩላቸው፣ “ይህ ከሁለት ኩባንያዎች አጋርነት በላይ ነው፤ ይህም ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሰውን ልጅ አቅም ለማሳደግ እና የበለጠ የተሳሰረችና የበለፀገች አፍሪካን ለመፍጠር ያለን ቁርጠኝነት ነው” ብለዋል።

በተጨማሪም ሁለቱ ኩባንያዎች አሁን ያለውን ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አቅም ለማሳደግ እና በሌሎች ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ያለውን ሰፊ መሠረተ ልማትና ቴክኒካዊ ብቃት በመጠቀም በዓለም አቀፍ የዲጂታል ገበያ አዳዲስ ዕድሎችን ለመክፈት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories