በሶማሊያ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የረሃብ መከላከያ ተቋም በገንዘብ እጥረት ምክንያት ሊዘጋ እንደሚችል ተገለጸ

በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም በሚቀጥሉት ወራት ከዓለም አቀፍ ለጋሾች 90 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ካልቻለ፣ በሚያዝያ ወር ሥራውን ለማቆም እንደሚገደድ አስጠነቀቀ።

ምንም እንኳን ተቋሙ ባለፈው ሳምንት ከአውሮፓ ህብረት የ6.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ቢያገኝም፣ ይህም ድጋፍ ካጋጠመው ከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ አንጻር እጅግ አነስተኛ መሆኑ ተገልጿል።

 ተቋሙ እ.ኤ.አ በ2024 ከለጋሾች ያገኘው 450 ሚሊዮን ዶላር የነበረ ቢሆንም፣ ባለፈው ዓመት ግን ይህ ቁጥር ወደ 100 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ብሏል።

ይህም የሆነው አሜሪካን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት ለሰብአዊ እርዳታ የሚመድቡትን በጀት በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሳቸው እንደሆነ ተመልክቷል።

በሶማሊያ እ.ኤ.አ በ2022 እና በ2023 የተከሰተውና ላለፉት 40 ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ የተባለው ድርቅ፣ እስካሁን 4.5 ሚሊዮን ሰዎችን ለከፋ የምግብ እጥረት ዳርጓል። ከእነዚህም መካከል 1.8 ሚሊዮን የሚሆኑት ሕፃናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጋለጡ ናቸው።

 የዓለም የምግብ ፕሮግራም እንደሚለው ከሆነ፣ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሚገኘው የገንዘብ ድጋፍ ሶማሊያ ካለችበት ችግር መውጣቷን ወይም ወደ የከፋ አደጋ ማምራቷን ይወስናል።

 በተመሳሳይ ሁኔታ በኡጋንዳ የሚገኙ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ስደተኞችም በተመሳሳይ የገንዘብ እጥረት ምክንያት መሠረታዊ የጤና እና የምግብ አቅርቦት እያጡ መሆናቸው ተገልጿል።

ይህ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለድሃ ሀገራት የሚሰጠው የልማት እና የሰብአዊ እርዳታ ፖሊሲ በአስቸኳይ እንዲሻሻል ጥሪዎች እንዲቀርቡ አድርጓል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories