የኢትዮጵያ የቡና ዘርፍ የአውሮፓን ህብረት የደን ጥበቃ መስፈርት ለማሟላት ተጨባጭ እድገት ማሳየቱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የቡና ዘርፍ በአውሮፓ ህብረት የወጣውን አዲስ የደን ጭፍጨፋ ነፃ የአቅርቦት ሰንሰለት ደንብ (EUDR) ለማሟላት ተጨባጭ እድገት እያሳየ መሆኑን የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ።

ህብረቱ  እንዳስታወቀው፣ በዋና ዋና የቡና አምራች አካባቢዎች እየተከናወነ ያለው የዲጂታል መረጃ አሰባሰብ እና የመሬት ይዞታ ምዝገባ ሂደት ለዚህ ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁሟል።

 የኖርዌይ ልማት ፈንድ ባዘጋጀው እና ከ60 በላይ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት የምክክር መድረክ ላይ፣ የኢትዮጵያ የቡና እሴት ሰንሰለት ከደን ጭፍጨፋ ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸው ተገምግሟል።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ የቡድን መሪ ጁሊያ ዋልሼባወር እንደገለጹት፣ በቡና አምራች ወረዳዎች እየተዘረጉ ያሉ የዲጂታል መከታተያ ስርዓቶች እና የካዳስተር (የመሬት ምዝገባ) አሰራሮች ቡናው የት እንደተመረተ በትክክል ለማረጋገጥ ያስችላሉ።

 ይህም ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ገበያ የምትልከው ቡና ለአካባቢ ጥበቃ ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን ለተጠቃሚዎች ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ያጠናክረዋል።

ይሁን እንጂ አሁንም እንደ ትክክለኛ የካርታ መረጃ አቅርቦት እና ከእርሻ እስከ ውጭ ንግድ ያለውን ረጅም ሰንሰለት በዝርዝር የመከታተል ተግዳሮቶች መኖራቸውንና ለዚህም ተግባራዊ መፍትሄዎች እንደሚያስፈልጉ ተጠቁሟል።

እ.ኤ.አ. በ2023 የጸደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ደንብ (EUDR)፣ እንደ ቡና ያሉ ምርቶች ከታህሳስ 2020 በኋላ ደን በተመነጠረበት መሬት ላይ ያልተመረቱ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይጠይቃል።

ይህ ሕግ መጀመሪያ በ2025 መጨረሻ ተግባራዊ እንዲሆን ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የአውሮፓ ፓርላማ የትግበራ ጊዜውን በአንድ ዓመት አራዝሞታል።

 በዚህም መሠረት ትላልቅ ላኪዎች እስከ ታህሳስ 2026፣ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች ደግሞ እስከ ሰኔ 2027 ድረስ መስፈርቱን አሟልተው እንዲገኙ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories