ዝቅተኛ ተሳታፊ የታየበት የመሬት ጨረታ ከፍተኛ ገንዘብ ቀረበበት

ለሚኩራ የሚገኝ 500 ካሬ ሜትር መሬት 6.5 ሚሊየን ብር ተሸጧል

በኢቢቪ ዘጋቢ

ባሳለፍነው ሳምንት በተደረገ የ8ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጨረታ ያቀረበው የመሬት ብዛት ከቀደመው ጨረታ ያነሰ እንዲሁም ዝቅተኛ የተጫራች ቁጥር የተመዘገበበት ቢሆን ከፍተኛ ዋጋ የቀረበበት ሆኗል፡፡

ለበጀት አመቱ 3ኛ በሆነው ባሳለፍነው ሳምንት በተደረገው የመሬት ሊዝ ጨረታ የከተማ አስተዳደሩ በጠቅላላው 39 ሺ 6 መቶ ካሬ ሜትር የሚሆኑ 134 ቦታዎች በ 8 ክፍለ ከተማዎች ለሽያጭ ቀርበው ነበር፡፡

ይህ መጠን ከ3 ወራት በፊት ለጨረታ ቀርቦ ከነበረው 70 ሺ ካሬ ሜትር ካላቸው 274 ቦታዎች አንፃር ቅናሽ የታየበት ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ታህሳስ ላይ ባወጣው ጨረታ ተጠቅሶ ከነበረው የመሬት ብዛት አንጻር በዋናነነት ልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኙ በ86 ቦታዎች በህግ እና ባለቤትነት ክርክር ውስጥ የሚገኙ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ለልማት የሚፈልጋቸው ሆነው የተገኙ በታዎች ተቀንሰዋል፡፡

እንዲያም ሆኖ ጨረታው የተሳትፍ ቅናሽ ያስተነገደ ቢሆንም ከቀደመው ጨረታ አንጻር ከፍተኛ ዋጋ እንደቀረበበት ነው ፎርቹን ያስነበበው፡፡

በጨረታው 2 ሺ 67 ተጫራቾች መሬት ለመግዛት ፍላጎት ያሳዩ መሆኑ የታወቀ ሱሆን በቀደመው ጨረታ ከተሳተፉ 3ሺ 255 ተጫራቾች አንፃር ዝቅ ያለ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በኮልፌ ቀራኒዮ ለቀረበ 167 ካ.ሜ ቦታ ኡመር ይብሬ የተባሉ ግለሰብ ወደ 26 ሚሊየን 65 ሺ ብር ገደማ ማሸነፊያ ዋጋ በማቅረብ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረቡ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ግለሰቡ በካሬ ሜትር 156 ሺ 80 ብር ያቀረቡ መሆኑ ሲታይ ይህ ዋጋ ከ3 ወራት በፊት ተደርጎ በነበረው ጨረታ ቀርቦ ከነበረው ከፍተኛ ዋጋ (135 ሺብር) አንጻር የ16 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ነው፡፡

ለበጀት አመቱ ሶስተኛ በሆነው ጨረታ ከቀደመው ጨረታ አንጻር በተመሳሳይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የቀረበ ሌላ 186 ካ.ሜ ቦታ 135 ሺ 300 ብር ቀርቦበት ከፍተኛ ዋጋ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡  

ሁልጊዜ እንደሚታየው አነስ ላሉ ቦታዎች ከፍተኛ ፉክክር እና ዋጋ የሚቀርብባቸው ሲሆን፤ ባንጻሩ ሰፋ ያሉ በታዎች ዝቅ ያለ ዋጋ እንደቀረበባቸው ታውቋል፡፡

ለዚህ ጥሩ ማሳያ ለሚ ኩራ ላይ 500 ካ.ሜ ቦታ በካሬ ሜትር 13 ሺ 101 ብር ወይም በጠቅላላው 6 ሚሊየን 550 ብር ተሸጧል፡፡

ሰሚት 72 አካባቢ 130 ካ.ሜ ለሆነ ቦታ 110 ተጫራቾች የተሳተፉ ሲሆን አሸናፊ የሆነው ዋጋ በካሬ ሜትር 126 ሺ ብር ሆኗል፡፡

ለነገሩ ለሚ ኩራ ለቀረቡ ቦታዎች ከሌሎች ክፍለ ከተማዎች አንጻር ከፍተኛ የተጫራች ፍላጎት ታይቷል፡፡©SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories