በአለምሰገድ እስጢፋኖስ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለቅዳሜ ገበያ እንዳስታወቀው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ የሚከናወነው የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ባወጣው “የኤሌክትሪክ ታሪፍ መወሰኛ መመሪያ ቁጥር008/2012 ዓ.ም” መሰረት ነው፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሽያጭና ደንበኞች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ይሄይስ ሥዩም እንደገለጹት በ2017 ዓ.ም ተግባራዊ የተደረገው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ የመኖሪያ ቤት፣ የንግድ፣ የማህበራዊ፣አነስተኛና መካከለኛ ኢንዲስትሪ ያካተተ አራት የታሪፍ መደቦች ተግባራዊ እየተደረገ ነው፡፡
ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ በየሩብ ዓመቱ ተከፋፍሎ ለአራት ዓመታት የሚተገበር እንደሆነ ለቅዳሜ ገበያ ተናግረዋል፡፡
የታሪፍ ማሻሻያው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግብዓቶችን በበቂ ሁኔታ ለማሟሟላት፣ አስተማማኝና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲኖር በማድረግ የኤሌክትሪከ ተደራሽነትን ለማስፋትና ቀጣይነት ያለው የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ዝርጋታ እና የመልሶ ግንባታ ስራዎችን ለማከናወን ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር የተቋሙን ገቢ ለማሳደግ እና ተወዳዳሪ የሆነ ተቋም ለመፍጠር እንደሚረዳ ጠቁመው ተቋሙ አቅሙን በማሳደግ ተደራሽነቱን ለማስፋት ወቅቱን የጠበቀ የታሪፍ ማሻሻያ እያደረገ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
የታሪፍ ማሻሻያው በወርሀዊ ሂሳብ ክፍያ ላይ ለውጥ ማምጣቱ እንደማይቀር የተናገሩት አቶ ይሄይስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ሀይል አጠቃቀም ፍጆታቸውን ማስተካከል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡@SECO


