የኡጋንዳ አየር መንገድን ለመታደግ አንጋፋው አቪዬተር አቶ ግርማ ዋቄ በጊዜያዊነት ተሾሙ

​የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፣ በአገሪቱ ብሔራዊ አየር መንገድ ውስጥ የሚታዩ የአመራር እና የአሠራር ድክመቶችን ለመቅረፍ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ግርማ ዋቄን በጊዜያዊ ሥራ አስፈፃሚነት እና በአማካሪነት ሾሙ።

ፕሬዝዳንቱ ለትራንስፖርት ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ፣ በአሁኑ ወቅት አየር መንገዱን በዋና ሥራ አስፈፃሚነት እየመሩ ያሉት ጄኒፈር ባሙቱራኪ ወዲያውኑ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱና የአየር መንገዱን አመራር ለአቶ ግርማ ዋቄ እና ለቦርዱ እንዲያስረክቡ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

​አቶ ግርማ ዋቄ አየር መንገዱን በጊዜያዊነት እስከ ሐምሌ 2026 ዓ.ም ድረስ የሚመሩ ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ ቋሚ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የመፈለጉን ሂደት በበላይነት ከመምራት ባለፈ አየር መንገዱ ያለበትን የአሠራር እና የአስተዳደር ችግሮች የማስተካከል ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

 የኡጋንዳ አየር መንገድ እ.ኤ.አ በ2019 ሥራ ከጀመረ አንስቶ በከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ፣ በግዥ ሂደት ግልጽነት ማጣት እና በአመራር ብቃት ማነስ ሲተች መቆየቱ የሚታወስ ነው።

​አቶ ግርማ ዋቄ ከ2004 እስከ 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በዋና ሥራ አስፈፃሚነት በገነቡበት ወቅት፣ አየር መንገዱን በአፍሪካ ግዙፍ እና ትርፋማ እንዲሆን በማድረጋቸው ትልቅ ስም ያተረፉ ባለሙያ ናቸው።

የኡጋንዳ መንግስት ይህንን የአቶ ግርማን ሰፊ ልምድ በመጠቀም አየር መንገዱን ወደ ተሻለ የንግድ መስመር ለመመለስና አስተማማኝ የአስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋት ተስፋ አድርጓል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories