የቴክኖሎጂ ግዙፍ አካላት ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ውጭ የራሳቸውን የኃይል ማመንጫዎች መገንባት ጀመሩ

በአሁኑ ወቅት የመረጃ ማዕከል አልሚዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት  እድገት ተከትሎ የሚመጣውን ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ለማርካት፣ ከሀገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ግሪድ  ውጭ የሆኑ የግል የተፈጥሮ ጋዝ ኃይል ማመንጫዎችን መገንባት መጀመራቸው ተዘግቧል።

“ጥላ ግሪድ” ተብሎ የተጠራው ይህ አሰራር፣ ኩባንያዎች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታን ለመጠበቅ የሚፈጅባቸውን ረጅም ዓመታት ለማሳጠርና አሁን ያለውን የግሪድ መጣበብ ለመሸሸግ የመረጡት አማራጭ ሆኗል።

በቴክሳስ ግዛት እየተገነባ ያለው የGW Ranch ፕሮጀክት የዚህ አዲስ አካሄድ ዋነኛ ማሳያ ሲሆን፣ ይህ ፕሮጀክት ብቻውን እንደ ቺካጎ ያሉ ታላላቅ ከተሞች የሚጠቀሙትን ያህል የኤሌክትሪክ ኃይል ይፈልጋል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ ከተለመደው የኤሌክትሪክ መስመር ጋር ሳይገናኝ የተፈጥሮ ጋዝ ተርባይኖችን እና የፀሐይ ብርሃን ኃይልን በመጠቀም ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ ነው።

 በተመሳሳይ ሁኔታ በዌስት ቨርጂኒያ የሚገኝ ሌላ ፕሮጀክት ለ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ሊበቃ የሚችል የተፈጥሮ ጋዝ ፍላጎት እንዳለው ተጠቁሟል።

የኃይል ፍላጎት ተቆጣጣሪው ክላንቪዉ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፣ በአሁኑ ወቅት በመላው አሜሪካ ቢያንስ 47 የሚሆኑ የመረጃ ማዕከል ፕሮጀክቶች በዚህ “ጥላ ግሪድ” መልክ እየተገነቡ ይገኛሉ።

 ምንም እንኳን ይህ አካሄድ በየአካባቢው ባሉ ነዋሪዎች ላይ የሚፈጠረውን የኃይል እጥረትና የዋጋ ንረት ይቀንሳል ተብሎ ቢታሰብም፣ በሌላ በኩል ከፍተኛ የአካባቢ ብክለትና የካርቦን ልቀት እንደሚያስከትል ተመራማሪዎች ያስጠነቅቃሉ።

በተለይ የተፈጥሮ ጋዝ አጠቃቀሙ ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ግቦች እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።

የክላንቪዉ ተመራማሪ የሆኑት ማይክል ቶማስ ሁኔታውን “ለአየር ንብረት ግቦች አስከፊ” ሲሉ ገልጸውታል። ኩባንያዎቹ ግን የንግድ ውድድሩን ለማሸነፍና የAI መሠረተ ልማታቸውን በፍጥነት ለማስፋፋት ሲሉ እነዚህን የግል ኃይል ማመንጫዎች እንደ ብቸኛ አማራጭ እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories