የአውሮፓ ኅብረት የንግድ ኮሚሽነር ማሮስ ሴፍኮቪች የቻይና ኩባንያዎች በአውሮፓ ገበያ በአነስተኛ ታሪፍ የመጠቀም ዕድላቸው የቻይና ኢኮኖሚ ለአውሮፓ ንግዶች በሚኖረው ክፍትነት ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።
ባለፈው ዓመት የአውሮፓ ኅብረት ከቻይና ጋር ያለው የንግድ ጉድለት 359 ቢሊዮን ዩሮ የደረሰ ሲሆን፣ ይህ አኃዝ በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛውና ቀጣይነት ሊኖረው የማይችል ደረጃ ላይ መሆኑን ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።
ሴፍኮቪች በቆጵሮስ በተካሄደው የንግድ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት፣ አንዳንድ የዓለም የንግድ ድርጅት አባላት የገዛ ገበያቸውን ዝግ በማድረግ በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ ያላቸውን ድርሻ በከፍተኛ ሁኔታ ማስፋፋታቸው ፍትሐዊ ስላልሆነ፣ በታሪፍ ጥቅማጥቅም እና በገበያ ክፍትነት መካከል ግልጽ ትስስር ሊኖር ይገባል።
ከቻይና ጋር በተደረጉ ግንኙነቶች እንደ ውድ ማዕድናት የኤክስፖርት ፈቃድ ላይ የተወሰኑ ውጤቶች ቢታዩም፣ ለረጅም ጊዜ የቆዩ መዋቅራዊ መዛባቶች አሁንም መኖራቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፣ በቀጣይ ወር በካሜሩን በሚካሄደው የዓለም የንግድ ድርጅት ስብሰባ ላይ ስለ ሥርዓቱ አሠራር ጥብቅ ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል።@SECO


