ዛምቢያ፣ አንጎላ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሎቢቶ ኮሪደርን ልማት ለማፋጠን ስምምነት ላይ ደረሱ። በሉዋንዳ በተካሄደው የሦስቱ አገራት የገንዘብ፣ የትራንስፖርት እና የንግድ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ኅብረት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የዓለም ባንክ እንዲሁም የአሜሪካና የጃፓን ተወካዮች ተገኝተዋል።
ይህ ስትራቴጂያዊ የትራንስፖርት መስመር ከ30 ሚሊዮን በላይ ሕዝብን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በተለይም እንደ ኮፐር እና ኮባልት ያሉ ወሳኝ ማዕድናትን ወደ ዓለም ገበያ ለማቅረብ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
ስብሰባው የጋራ የኢንቨስትመንት መድረክ ለመፍጠር እና የግል ባለሀብቶችን ለማሳተፍ የሚያስችል መሪ ዕቅድ አጽድቋል።@SECO


