የዓለም የምግብ ፕሮግራም በሶማሊያ “አሰቃቂ የረሃብ ቀውስ” ሊከሰት እንደሚችል አስጠነቀቀ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም በሶማሊያ እጅግ አሳሳቢ የሆነ የገንዘብ ድጋፍ እጥረት መከሰቱን ተከትሎ፣ በአገሪቱ በሚገኙ 4.4 ሚሊዮን ዜጎች ላይ “አሰቃቂ የረሃብ አደጋ” ሊጋረጥ እንደሚችል አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

 የድርጅቱ የአደጋ ጊዜ ዝግጅት እና ምላሽ ዳይሬክተር ሮስ ስሚዝ በመቅዲሾ በሰጡት መግለጫ፣ የዓለም ማህበረሰብ በሶማሊያ ለሚሰቃዩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች፣ ወንዶች እና ሕፃናት ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

 እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ድርጅቱ ያለው የገንዘብ ክምችት በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሚያልቅ በመሆኑ፣ ሕይወት አድን የሆኑ የምግብ እና የሥርዓተ-ምግብ እርዳታዎች ሙሉ በሙሉ የመቋረጥ አደጋ ተጋርጦባቸዋል።

ይህ አስከፊ ሁኔታ የተከሰተው ሶማሊያ ለሁለት ተከታታይ ወቅቶች ዝናብ በማጣቷ፣ ሰብሎች በመውደማቸው እና ከብቶች በማለቃቸው ምክንያት የሶማሊያ መንግሥት ብሔራዊ የድርቅ የአደጋ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት ወቅት ነው። በሀገሪቱ ያለው ግጭት እና ዓለም አቀፍ የረድኤት ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ቀውሱን ይበልጥ አባብሶታል።ድርጅቱ እ.ኤ.አ. በ2025 መጀመሪያ ላይ ለ2.2 ሚሊዮን ሰዎች እርዳታ ያቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ በገንዘብ እጥረት ምክንያት አሁን ላይ ድጋፍ የሚያገኙት ሰዎች ቁጥር ወደ 600,000 ዝቅ እንዲል ተገዷል። ይህም ማለት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ያለምንም እርዳታ ለረሃብ ተጋልጠዋል ማለት ነው።

ተቋሙ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት (ከመጋቢት እስከ ነሐሴ) ለተረጂዎች የሚሆን ምግብ ለማቅረብ በአስቸኳይ 95 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚፈልግ አስታውቋል። ይህ የገንዘብ ድጋፍ በአፋጣኝ ካልተገኘ ግን እስከ መጪው ሚያዝያ ወር ድረስ ሰብአዊ እርዳታውን ሙሉ በሙሉ ለማቆም እንደሚገደድ አስጥንቅቋል።

ሁኔታው እ.ኤ.አ. በ2022 ዓለም አቀፍ ድጋፍ ተረባርቦ የረሃብ አደጋ በጠባቡ ከተቀለበሰበት ወቅት ጋር ተመሳሳይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ አሁኑኑ እርምጃ ካልተወሰደ ግን በረሃብ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊያገጭ እንደሚችል ተገልጿል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories