በኢቪቢ ዘጋቢ
የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንደገለጹት፣ በተደረገው የጋራ ገቢዎች ክፍፍል ቀመር ማሻሻያ ምክንያት የክልሎች ድርሻ ከነበረበት 4.2 ቢሊዮን ብር ወደ 91.73 ቢሊዮን ብር አድጓል።
በ2017 በጀት ዓመት 91.73 ቢሊዮን ብር ለክልሎች የተላለፈ ሲሆን፣ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሰባት ወራት ደግሞ 71.33 ቢሊዮን ብር መተላለፉን አፈ ጉባኤው አብራርተዋል።
ይህ የተገለጸው ምክር ቤቱ ከገቢዎችና ከማዕድን ሚኒስቴር የኦዲት ሪፖርት ግኝቶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው።@SECO


