ጎልድማን ሳክስ በቅርቡ ይፋ ባደረገው የትንተና ሪፖርት፣ የዓለም የነዳጅ ገበያ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ መዋዠቅ እንደሚያስተናግድና እ.ኤ.አ. በ2027 ዋጋው በከፍተኛ ሁኔታ ሊያገግም እንደሚችል አስታወቀ።
ባንኩ እስከ 2027 ማብቂያ ድረስ ያለውን የነዳጅ ዋጋ አቅጣጫ በዝርዝር አስቀምጧል። እንደ ጎልድማን ሳክስ ትንበያ ከሆነ፣ እ.ኤ.አ. በ2026 አራተኛ ሩብ ዓመት የነዳጅ ዋጋ መጠነኛ መሻሻል ያሳያል።
በዚህም መሠረት የብሬንት ክሩድ ዋጋ በአንድ በርሜል 60 ዶላር፣ የዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዲየት (የWTI) ደግሞ 56 ዶላር እንደሚደርስ ይጠበቃል።
ይህ የዋጋ ማሻሻያ የተደረገው በበለጸጉት አገራት ያለው የነዳጅ ክምችት በመቀነሱ ቢሆንም፣ ባንኩ ግን በ2026 በገበያው ላይ የነዳጅ ምርት ትርፍ ሊኖር እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል።
ይህም ማለት ምንም እንኳን የክምችት መጠን ቢቀንስም፣ አቅርቦቱ ከፍላጎቱ ስለሚበልጥ በ2026 ዋጋው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ጫና ሊያርፍበት ይችላል።
በዓመቱ አጋማሽ ላይ የብሬንት ክሩድ ዋጋ በአማካይ 65 ዶላር ይደርሳል ተብሎ የሚታሰብ ሲሆን፣ እስከ ታኅሣሥ 2027 ባለው ጊዜ ውስጥ ግን ዋጋው ወደ 70 ዶላር ከፍ ሊል እንደሚችል ተጠቁሟል። በተመሳሳይ የWTI ዋጋም ወደ 66 ዶላር ያድጋል ተብሏል።
ለዚህ የዋጋ ጭማሪ በምክንያትነት የተጠቀሱት ዋና ዋና ነጥቦች፦
የፍላጎት ዕድገት፦ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ።
የአቅርቦት መቀዛቀዝ፦ ከኦፔክ አባል አገራት ውጭ የሚመረተው ነዳጅ ዕድገት ፍጥነት መቀነሱ።
የገበያ ሚዛን መመለስ፦ ፍላጎትና አቅርቦት ተመጣጣኝ እየሆኑ መምጣታቸው ለዋጋው መጨመር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
ምንም እንኳን የዋጋ ጭማሪው ቢተነበይም፣ ባንኩ የጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ሁኔታውን ሊቀይሩት እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። በተለይም በኢራን እና በሩሲያ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች የሚላሉ ከሆነ፣ የነዳጅ አቅርቦት በገበያው ላይ ስለሚጥለቀለቅ ዋጋው አሁን ከተገመተው በ 5 እስከ 8 ዶላር ዝቅ ሊል ይችላል።
የነዳጅ ገበያው በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ በክምችት መጠን፣ በዓለም አቀፍ ፖሊሲዎች እና በአቅርቦት ሚዛን መካከል በሚደረግ ስስ ትግል ውስጥ እንደሚያልፍ ይጠበቃል።
2026 ዓ.ም የዋጋ ጫና የሚታይበት ዓመት ቢሆንም፣ 2027 ግን ገበያው ተረጋግቶ ዋጋው ወደ 70 ዶላር የሚጠጋበት ዓመት እንደሚሆን ጎልድማን ሳክስ ትንበያውን አጠቃሏል።@SECO


