የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዲሶቹ የኢራን መሪዎች የውይይት ጥያቄ ማቅረባቸውንና እሳቸውም ለመነጋገር መስማማታቸውን አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን የገለጹት ከአትላንቲክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።
ትራምፕ በፍሎሪዳ በሚገኘው መኖሪያቸው ሆነው ለጋዜጣው እንደተናገሩት፣ የኢራን ባለሥልጣናት አሁን ላይ የንግግር ፍላጎት አሳይተዋል።
“ሊያናግሩኝ ይፈልጋሉ፤ እኔም ለመነጋገር ተስማምቻለሁ። ስለዚህ አነጋግራቸዋለሁ፣” ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ኢራን ይህንን እርምጃ ቀደም ብላ መውሰድ እንደነበረባት በመጥቀስ ወቀሳ ሰንዝረዋል። “ይህንን ቀደም ብለው ማድረግ ነበረባቸው። በጣም ቀላል እና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ቀድመው ማቅረብ ይገባቸው ነበር፤ አሁን ግን በጣም ዘግይተዋል፣” ብለዋል።
ይህ የትራምፕ መግለጫ የወጣው በኢራን ከፍተኛ አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ አገሪቱ በአዲስ አመራር ስር ባለችበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጎታል።@SECO


