ጃምቦ ኮንስትራክሽን በጀንቦሮ ሪል ስቴት ላይ ክስ መሰረተ

ከሳሽ ጃምቦ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለንግድና ኢንቨስትመንት ምድብ 1ኛ ንግድ ችሎት በጀንቦሮ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማ ላይ ነው ክሱን የመሰረተው፡፡

ጃምቦ ኮንስትራክሽን በክሱ ላይ እንዳስታወቀው  ድርጅቱ ለረዥም ዓመታት በኮንስትራክሽንና በሪል ስቴት ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡:: ከሳሽ የንግድ ምልክቱን በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በማመልከቻ ቁጥር LTM/9061 በዓለም አቀፍ ምድብ 36 እና 37 እንዲሁም በማመልከቻ ቁጥርLTM/9654 በምድብ 36 አስመዝግቦ ጥበቃ እንዳለው ገልጿል፡፡

ነገር ግን ተከሳሽ ጀንቦሮ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማ በማለት በተመሳሳይ ዘርፍ እንደሚጠቀምና  ይህ ደግሞ በድምጸት ፣ በአጻጻፍ እንዲሁም በቅላጼ ከሳሽ ካስመዘገበው ጋር አብሮ ግርታን የሚፈጥር በመሆኑ ተከሳሽ ይህንን ስያሜ መጠቀም እንዲያቆም ጠይቋል፡፡

ተከሳሽ ጀንቦሮ ሪል ስቴት የሚለውን በመጠቀሙ ምክንያት በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ላይ መሳከር እየፈጠረና በንግድ ምልክቱ ምክንያት የገንዘብ መጠኑ  አንድ ሚሊዮን ብር  ኪሳራ አድርሶብኛል ሲልጃንቦ ኮንስትራክሽን  ክስ መስርቷል፡፡

 ተከሳሽ ጀንቦሮ ሪል ስቴት በሚል ስያሜ መጠቀም እንዲያቆም ሲል ከሳሽ ጨምሮ ጠይቋል፡፡

ተከሳሽ ጀንቦሮ ሪል ስቴት  በሪል ስቴት ሰራ ተሰማርቶ መስራት የጀመረውና የንግድ ፈቃድ ያወጣው በ 1/10/2012 ዓ.ም እንደሆነና ነገር ግን ተከሳሽ ጉዳት አድርሷል በተባለበት ስም መጠቀም ከጀመረ ከስድስት ዓማት በኋላ ከሳሽ ክስ ማቅረቡ በሕጉ በተቀመጠው ጊዜ ክሱን አለማቅረቡን የሚየሳይ በመሆኑ የቀረበው ክስ በይርጋ ሊታገድ የሚገባው ነው ሲል ተከራክሯል፡፡@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories