በዓለምሰገድ እስጢፋኖስ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) እንዳስታወቁት በ4ኛው ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የኢትዮጵያን ያላትን ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር በስፋት የሚያሳይ እና የማከሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የፈጠረውን ምቹ የኢንቨስትመንት እድል በስፋት ይተዋወቃሉ ።
ባለፈው አመት የተካሄደው 3ተኛው በኢትዮጱያ ኢንቨስት ያድርጉ አለም አቀፍ ፎረም በማዕድንና በሶላር ምርት የተሳተፉ 5 ድርጅቶች በ1.6 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መፈራረማቸውን ጠቁመው ድርጅቶቹ ወደ ስራ ገብተው ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ እያቀረቡ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
በ4ተኛው በኢትዮጱያ ኢንቨስት ያድርጉ አለም አቀፍ ፎረምም ከ2.6ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያወጡ ስምምነቶችን ለመፈራረም መታቀዱን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
በፎረሙ ላይ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና፣ በማዕድን፣ በታዳሽ ኃይል፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በቱሪዝም ዘርፎች ላይ ያተኮሩ የጎንዮሽ ውይይቶችና የንግድ ለንግድ ትስስሮች ይከናወናሉ።
ፎረሙ “ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ዝግጁ ናት በሚል መሪ ቃል በስካይ ላይት ሆቴል መጋቢት 17 እና 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄድ ሲሆን ከ800 በላይ ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች፣ የንግድ መሪዎች ፖሊሲ አውጪዎች እና የልማት አጋሮች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።@SECO


