በመካከለኛው ምስራቅ በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ወታደራዊ ውጥረት ተባብሶ ቢቀጥልም፣ የዓለም አቀፍ የወርቅ ዋጋ ማክሰኞ ዕለት የ4% ድንገተኛ ቅናሽ አሳይቷል።
የወርቅ ዋጋ በኦንስ ወደ $5,150.89 ዝቅ ማለቱ የታየው፣ ባለሀብቶች ከወርቅ ይልቅ የአሜሪካን ዶላር እንደ አስተማማኝ መጠለያ መምረጣቸውን ተከትሎ ዶላር ላለፉት ጥቂት ወራት ካልታየበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ነው።
በተጨማሪም የኢራን አብዮታዊ ዘበኛ የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ መዘጋቱን ማስታወቁን ተከትሎ የነዳጅ ማጓጓዣ ዋጋ መጨመሩ የዋጋ ግሽበት ስጋትን የፈጠረ ሲሆን፣ ይህም የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ የወለድ መጠንን ላያቀንስ ይችላል የሚል ግምት እንዲሰፍን አድርጓል።
ይህ የዶላር መጠናከርና የወለድ መጠን መጨመር ስጋት በወርቅ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ማዕድናትም ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ ሲሆን፣ የብር ዋጋ በ9.1%፣ የፕላቲኒየም ደግሞ በ11.7% እንዲቀንሱ ምክንያት ሆኗል።
ሆኖም የጂኦፖለቲካዊ ግጭቱ ካልረገበ የወርቅ ዋጋ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ እስከ $5,600 ሊደርስ እንደሚችል ተንታኞች እየገለጹ ይገኛሉ።@SECO


